Asset Publisher

ዜናዎች

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የማስተባበር ስራ ላከናወኑ ባለሙያዎች የምስጋና መርሃ ግብር አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር 37ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛውን የአስፈፃሚዎች ም/ቤት ስብሰባ ለመዘገብ የመጡ ጋዜጠኞችን ላስተባበሩ ለተቋሙ ባለሙያዎች የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን ለሚዘግቡ ጋዜጠኞች የመግቢያ ባጅ እየሰጠ ይገኛል

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን  ከኢፌዲሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር 37ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ  እና 44ኛውን የስራ አስፈፃሚዎች ስብሰባን ለመዘገብ ለሚመጡ  የውጭ  እና የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች  የመግቢያ  ባጅ (press pass) በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመገናኛ ብዙኃን ህጎች ዙሪያ ለሰራተኞቹ ስልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአለም አቀፍ እና በሀገር  አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ህጎች እንዲሁም ተያያዥ ህጎች ዙሪያ   ለሰራተኞቹ ስልጠና ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የ6ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ባለፋት 6ወራት ባከናወኗቸው ተግባራት ላይ ውይይት አካሂደዋል።

ባለሥልጣኑ ከማስታወቂያ ዘርፍ አካላት ጋር ዘርፉን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባለፉት ስድስት ወራት በማስታወቂያ ክትትል ውጤቶች ላይ እንዲሁም  ዘርፉን ማሳደግ በሚቻልባቸው  ጉዳዮች ዙሪያ ከመገናኛ ብዙኃን የማስታወቂያ ክፍል አመራሮች፣ ከማስታወቂያ  ድርጅት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር  ውይይት አካሂዷል፡፡

ባለሥልጣኑ ለበይነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን  በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ  መከላከያ መንገዶች ዙሪያ ለበይነመረብ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች  እና  አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

“ወጣቶች ነገ ላይ ከጥላቻ የፀዳች እና ሰላም የሰፈነባት ሀገርን ለመረከብ ዛሬ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን በንቃት መዋጋት ይኖርባቸዋል” አቶ መሐመድ እድሪስ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር

ወጣቶች ነገ ላይ ከጥላቻ የፀዳች እና ሰላም የሰፈነባት ሀገርን ለመረከብ ዛሬ ላይ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን በንቃት መዋጋት ይኖርባቸዋል ሲሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ተናገሩ፡፡

ባለሥልጣኑ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን በሚመለከት ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር ተወያየ፡፡ 

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ምሁር ዓይነ-ስውራን ሴቶች ማህበር ጋር በመተባበር የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነትን በማሳደግ ረገድ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን በሚመለከት ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን የመከላከል ስራ ለማከናወን የሚያስችል ስልጠና ለባለሥልጣኑ ባለሙያዎች  ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በሰው ሰራሽ አስተውሎት /አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ/ የታገዘ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን የመከላከል ስራ እንዲያከናውኑ ለባለሥልጣኑ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ክትትልና አቅም ግንባታ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

ባለሥልጣኑ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን በመከላከያ መንገዶች ዙሪያ ለ2ተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ከ11 ዱም ክ/ከተሞች ከሚገኙ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተወጣጡ የሚኒ ሚዲያ ተማሪዎች   በጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ መከላከያ መንገዶች ዙሪያ  ስልጠና ሰጠ፡፡

ባለሥልጣኑ በቴከኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓትን ከመዘርጋት እና ከሰው ሃብት ስምሪት አንፃር የሰራቸው ስራዎች ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቆመ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው ምልከታ ባለሥልጣኑ በቴከኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓትን ከመዘርጋት እንዲሁም ከሰው ሃብት ስምሪት አንፃር የሰራቸው ስራዎች ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተመላክቷል

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት አዎንታዊ አስተዋፅኦ  እንዲያበረክት መገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋፅኦ እንዲያበረክት መገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ  "ክህሎት ለሁለንተናዊ ስኬት" በሚል መሪ ሀሳብ ለመገናኛ ብዙኃን አመራሮችና ባለሙያዎች በተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ተጠቆመ፡፡

ባለሥልጣኑ ለሰራተኞቹ ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ለሰራተኞቹ  ስልጠና ሰጥቷል።

ባለሥልጣኑ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር የኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር የኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ባለሥልጣኑ ከጀስቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከጀስቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በመገናኛ ብዙኃን ሕጎች፣ በሙያ ስነ-ምግባር መርሆች እና በማህበረሰብ ብሮድካስት ሚና ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የእርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓትን ለማጠናከር የሚረዳ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ጋር ውይይት አካሄደ ፡፡

ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ  የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር "የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለአብሮነት እሴቶች መጠናከር" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

የኢ.መ.ብ.ባ የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ አዘጋገብን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ስልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ልማት ተቋም (Global Green Growth Institues) ጋር በመተባበር የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ አዘጋገብን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአረብኛ ቋንቋ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ስልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከአልጀዚራ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ውስጥ በአረብኛ ቋንቋ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ስርዓተ ፆታን ያገናዘበ የግጭት አዘጋገብ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

ባለሥልጣኑ ከ UN WOMEN ኢትዮጵያ ጋር በመተባባር ስርዓተ ፆታን ያገናዘበ የመገናኛ ብዙኃን የግጭት አዘጋገብ መመሪያ አዘጋጅቶ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡:

የኢ. መ.ብ.ባ የ3ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አድርጓል፡፤

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ባለፉት 9 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና የትምህርት እና ስልጠና ባለሥልጣን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት ሁለቱ ተቋማት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ ማስታዎቂያዎችን በተመለከተ በቅንጅት ለመስራት ነው።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከ UN Women ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በማስታወቂያ ዘርፉ የተሰማሩ የተለያዩ ባለሙያዎችን አሰለጠነ።

ኢ.መ.ብ.ባ ከ UN Women ጋር በመተባበር በስርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጭ ማስታወቂያ ዝግጅት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከህዝብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች  ጋር  ሚዲያዎች በሚያሰራጯቸው ፕሮግራሞች ላይ በሚያደርገው የክትትል ስራ ውጤት  ዙርያ ውይይት አካሄደ።

የኢ.መ.ብ.ባ የህዝብ እና የማህበረሰብ መገናኛ ክትትል ዳይሬክቶሬት የሚያከናውናቸውን የክትትል አግባቦችና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ከህዝብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ከፍተኛ አዘጋጆች ጋር ተወያየ።

ኢ.መ.ብ.ባ ሁለተኛ ዙር ለመከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ መርሐግብር አካሄደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች “ደማችንን ለመከላከያ ሰራዊታችን” በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ዙር ለመከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ መርሐግብር አካሄዱ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ኦን ፕሮሞሽን ኃ/የተ/የግ/ማ (On promotion PLC) በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካሄደው አለም አቀፉ የሚዲያ ኤክስፖ በጋራ ለማዘጋጀት በዛሬው እለት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ በስምምነቱ ወቅት እንደተናገሩት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚዲያውን ዘርፍ የሚያሳድጉ ኤክስፖዎች በተለያዩ ሀገራት ይካሄዳሉ፤ በሀገራችን ደረጃም አሁን መጀመሩ ለሚዲያው እድገት ትልቅ እምርታ ነው። ስለሆነም ቀጣይነት ባለው መልኩ በትብብር እንሰራለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በተቋሙ የ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ።

በውይይቱ የሩብ ዓመቱ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በእቅድ የተያዙ ስራዎች አፈጻጸማቸው ምን እንደሚመስል እንዲሁም የተገኙ ጠንካራ ጎኖች እና የተስተዋሉ ክፍተቶች በሪፖርቱ ተነስተዋል። ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ እንዲጠናከሩ እና የታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ደግሞ የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች የተለያዩ አስተያየቶችን በማንሳት እንዴት ማሻሻል እንደሚገባ እና ወደፊት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከUN WOMEN ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሥርዓተ ጾታ ምላሽ ሰጭ መመሪያ ዙሪያ እና የሴቶችን የውሳኔ ሰጪነት ሚናን ለማጎልበት የሶስት ቀን ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

የስልጠናው ዋና አላማ ሥርዓተ-ጾታን ያገናዘበ ምላሽ ሰጭ መመሪያ አተገባበር፤ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ሴት እና ወንድ ባለሙያዎች ስለሚያገኟቸው እና ስለሚያሰጧቸው ዕድሎች፤ መገናኛ ብዙኃን በይዘታቸው ወንዶች እና ሴቶችን የሚዘግቡበትና የሚቀርጹበት ዕይታ፤ የጋዜጠኞች ዘገባዎች የሁለቱም ጾታዎች ድምጽ እና ሃሳብ በእኩል መጠን ማስተናገድ ዙሪያ ላይ አቅም መገንባት ያተኮረ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የኤፍ.ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ ፕሮግራሞችን በቀጥታ ተቀብለው ማስተላለፍ ወይም ሊንክ ማድረግ ከዛሬ ጀምሮ የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የሬዲዮ ሞገድ በሀገራችን በጣም ውስን መሆኑ ይታወቃል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሬድዮ ባለፈቃዶች በማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እንዲሁም የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ይዘቶችን በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ መረጃ ተደራሽ ማድረግ አለባቸው። 

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ፍትህ ለሁሉም ኢትዮጵያ (Justice for All - P.F.E) በመገናኛ ብዙኃን እድገት ዙሪያ በጋራ ለመስራት በዛሬው ዕለት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

ተቋማቱ ከዚህ በፊት የሚዲያ ኢንዱስትሪውን እድገት አስመልክቶ የጋራ ጥናት አካሂደዋል፡፡ በመሆኑም በጥናቱ በተለዩ ጉዳዮች፣ በሚዲያ ሕጎችና አሰራሮች እንዲሁም በሚዲያ አቅም ግንባታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

— 30 Items per Page
Showing 1 - 30 of 45 results.