የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ሰላም ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራረመ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ሰላም ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራረመ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢ... የሰላም ሚኒስቴር ጋር መገናኛ ብዙኃን ሰላምን ለማስጠበቅ ያላቸዉን ሚና የሚያጠናክር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

በፊርማ ስነ- ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ መገናኛ ብዙኃን ለሰፊው የህብረተሰብ ክፍል ያላቸዉን ተደራሽነት ተጠቅመዉ  ሰላምን በማጠናከር ለሀገራዊ ግንባታ  ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ገልፀው ባለሥልጣኑ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እያከናወነ ባለዉ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ-ግብር ጥላቻን በመዋጋት አብሮነትን እና ሰላምን እያሰረፀ ይገኛል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለዉም መገናኛ ብዙኃን በህግ የተሰጣቸዉን ስልጣን እና ሀላፊነት በመጠቀም  ለሰላሙ የሚቆረቆር ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ  የሁለቱ ተቋማት በጋራ መስራት አስላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ / ከይረድን ተዘራ በበኩላቸዉ ማህረሰብ ላይ መስራት የሚቻለዉ መገናኛ ብዙኃን ግጭትን ከመተንተን ባለፈ አዎንታዊ  የሰላም ሀሳቦች ላይ በማተኮር የተረጋጋ ሀገር  ለመፍጠር  ዓይነተኛ ሚና ሲጫወቱ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዲኤታው አክለዉም ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጋር በጋራ መስራታችን  የሰላም ግንባታ  ሂደትን ከማጠናከሩም በላይ ለሀገራዊ ደህንነት  ያለዉ ፋይዳ የጎላ እንደሚሆን ገልፀዋል።

በስምምነቱ ወቅት ሁለቱ ተቋማት ሀገራዊ አንድነትና ብሔራዊ መግባባትን  ለማጠናከር የመገናኛ ብዙኃኑን አቅም ግንባታ ማጠናከር፣ ተደራሽነታቸዉን ማረጋገጥ፣ ብዝሀነትን የሚያጠናክሩ ዘገባዎች ማቅረባቸዉን መከታተል፣የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግሮችን ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ መድረክ መፍጠር እንዲሁም በዘርፉ አስፈላጊ የሆኑ ጥናቶችን በጋራ መስራት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡