ባለሥልጣኑ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን በሚመለከት ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር ተወያየ፡፡ 

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ባለሥልጣኑ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን በሚመለከት ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር ተወያየ፡፡ 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6/2016 ዓ.ም (ኢ.መ.ብ.ባ)

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ምሁር ዓይነ-ስውራን ሴቶች ማህበር ጋር በመተባበር የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነትን በማሳደግ ረገድ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን በሚመለከት ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት አካሄደ፡፡  

በውይይቱ ላይ የተገኙት የባለሥልጣኑ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ዱረቲ ታደሰ አካል ጉዳተኞችን በሚመለከት በማህረሰቡ ውስጥ የሚስተዋለውን የተዛባ አመለካከት በመቀየር ረገድ መገናኛ ብዙኃን   ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡  

የኢትዮጵያ ምሁር አይነ-ስውራን ሴቶች ማህበር ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ በቀለች ጥሩዬ በበኩላቸው ባለሥልጣኑ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከማህበሩ ጋር በመተባበር መድረኩን በማዘጋጀቱ ምስጋናቸውን ገልፀው ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ተግዳሮቶች ቢገጥመውም እስካሁን ድረስ ልዩ ልዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ እና በቀጣይም ማህበሩ ከመገናኛ ብዙኃን ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የአካል ጉዳተኞች   ተጠቃሚነትን በማሳደግ ረገድ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን በሚመለከት የመነሻ ሰነድ ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱም መገናኛ ብዙኃን የአካል ጉዳተኞችን በትምህርት፣ በስራና በሌሎች የማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና በፓለቲካዊ ጉዳዩች ላይ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ያገናዘበና የመረጃ ተደራሽነትን ያከበረ የሚዲያ ሽፋን በመስጠት የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተመላክቷል።