የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች ላይ ያተኮረ ሁለተኛ ዙር ስልጠና ሰጠ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች ላይ ያተኮረ ሁለተኛ ዙር ስልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተወጣጡ ሰልጣኞች በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች እንዲሁም በሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ዙሪያ ሁለተኛ ዙር ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በሰልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የሽወርቅ ግርማ  የስልጠናው ዋና ዓላማ ሰልጣኞች በመሰረታዊ ጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች ላይ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ እና ኃላፊነትን የተላበሰ የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት በማዳበር በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ  ራሳቸዉን ብሎም ሀገራቸዉን ከተዛቡ መረጃዎች እንዲጠብቁ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡

ኃላፊዋ አክለውም ሰልጣኞች በመሰረታዊ ጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች ላይ ግንዛቤ ከማሳደግ እና ኃላፊነትን የተላበሰ የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ከማዳበር በተጨማሪ የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ሂደት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡፡

ሰልጣኞች በበኩላቸው ስልጠናው መሰረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆዎችን እና ስነ ምግባርን እንድንረዳ እና የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎትን እንድናሳድግ ግንዛቤ ስለፈጠረልን በመገናኛ ብዙኃን ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃዎችን ስንመለከት ለባለሥልጣኑ በማሳወቅ እና በመጠቆም የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የዜጎችን ተሳትፎ እና የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት /Media literacy/ የሚያሳድጉ ዘዴዎችን ቀይሶ ዜጎች ራሳቸዉን፣ ቤተሰባቸዉን ብሎም ሀገራቸዉን ከሐሰተኛ መረጃ እንዲከላከሉ ለማስቻል የሚያግዙ ስልጠናዎችን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡