በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሲሰጥ የነበረዉ በሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ላይ ያተኮረ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተጠናቀቀ።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሲሰጥ የነበረዉ በሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ላይ ያተኮረ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተወጣጡ ሰልጣኞች በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች እንዲሁም በሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ዙሪያ በሁለት ክፍል ሲሰጥ የነበረዉ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተጠናቋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እንድሪስ ባለሥልጣኑ ይህንን ስልጠና ሲያዘጋጅ ሰልጣኞች የጋዜጠኝነት መርህን ፤ ስነ ምግባርን እና የሚዲያ አጠቀቃቀምን ካለመገንዘብ ጋር ተያይዞ  የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ  ራሳቸዉን ብሎም ሀገራቸዉን ከተዛቡ መረጃዎች እንዲጠብቁ ለማስቻል  ነው ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለዉም  ሰልጣኞች መሰረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆዎችን በመረዳት እና  የሚዲያ አጠቃቅም ክህሎትን በማሳደግ  በመገናኛ ብዙኃን ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃወችን በማሳወቅ እና በመጠቆም የበኩላችሁን ድርሻ እንደምትወጡ ተስፋ እናደርጋለንም ብለዋል፡፡

ሰልጣኖች በበኩላቸው ስልጠናው በጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆች እንዲሁም በሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ  ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልፀው የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ሂደት ጥቆማ በመስጠት ከባለሥልጣኑ እና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመስራት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቅም፤በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች፤በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች እና ስነ-ምግባር ዙሪያ በሁለት ዙር ስልጠናዉን  ለተካፈሉ ሰልጣኖች ስርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡