“ወጣቶች ነገ ላይ ከጥላቻ የፀዳች እና ሰላም የሰፈነባት ሀገርን ለመረከብ ዛሬ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን በንቃት መዋጋት ይኖርባቸዋል” አቶ መሐመድ እድሪስ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ወጣቶች ነገ ላይ ከጥላቻ የፀዳች እና ሰላም የሰፈነባት ሀገርን ለመረከብ ዛሬ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን በንቃት መዋጋት ይኖርባቸዋልአቶ መሐመድ እድሪስ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር

ወጣቶች ነገ ላይ ከጥላቻ የፀዳች እና ሰላም የሰፈነባት ሀገርን ለመረከብ ዛሬ ላይ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን በንቃት መዋጋት ይኖርባቸዋል ሲሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ተናገሩ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን የተናገሩት ባለሥልጣኑ ለሁለተኛ ጊዜ በጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከያ መንገዶች ዙሪያ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ /ቤቶች የሚኒ ሚዲያ አባላት ተማሪዎች ስልጠና በሰጠበት ወቅት ነው፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የቴክኖሎጂ እድገት ለመማር ማስተማር ሂደት መቀላጠፍ ጉልህ  አስተዋፅኦ ቢኖረውም ለስነ-ልቦና ጫና እና ለውጤት ማሽቆልቆል ከፍተኛ ሚና ስለሚኖረው ተማሪዎች እጃቸው ላይ ያለውን ቴክኖሎጂ በአግበቡ ሊጠቀሙበት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ስልጠናው ተማሪዎች የሚዲያና የመረጃ አጠቃቀም ክህሎታቸውን በማሳደግ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን በመከላከል ረገድ የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል እንደተዘጋጀ ተናግረው በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት  ለሌሎች ማካፍል እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

ሰልጣኝ ተማሪዎች በበኩላቸው ስልጠናው የሚዲያና የመረጃ አጠቃቀም ክህሎታቸውን በማሳድ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል፡

በስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ 11ዱም /ከተሞች ከሚገኙ 32 ሁለተኛ ደረጃ /ቤቶች የተውጣጡ 96 የሚኒ ሚዲያ አባላት ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡