የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን የመከላከል ስራ ለማከናወን የሚያስችል ስልጠና ለባለሥልጣኑ ባለሙያዎች  ሰጠ፡፡

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን የመከላከል ስራ ለማከናወን የሚያስችል ስልጠና ለባለሥልጣኑ ባለሙያዎች  ሰጠ፡፡

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 05/2016 ዓ.ም (ኢ.መ.ብ.ባ)

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በሰው ሰራሽ አስተውሎት /አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ/ የታገዘ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን የመከላከል ስራ እንዲያከናውኑ ለባለሥልጣኑ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ክትትልና አቅም ግንባታ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናውን የከፈቱት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ኃላፊ  አቶ ዴሬሳ ተረፈ በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ በቀላሉ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን የመከታተል ስራ ለማከናወን  ቅድሚያ የባለሙያዎችን አቅም መገንባት በማስፈለጉ ስልጠናው እንደተዘጋጀ ገልፀው ስልጠናው በበይነ መረብ አማካኝነት የሚስራጭ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን ለመከታተል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም ባለሙያዎቹ ከስልጠናው ያገኙትን  እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው የተሻለ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡

ስልጠናው ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ባለሥልጣኑ መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለባለሙያዎቹ እንደሚሰጥ በመድረኩ ተጠቅሷል፡፡