የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ጋር በማስታወቂያ ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ጋር በማስታወቂያ ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን  ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ጋር በአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቂያ ስርጭት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

በስምምነቱ ወቅት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጩ የተዛባ ይዘት ያላቸው ማስታወቂያዎች ህብረተሰብን እና ሀገርን ዋጋ ያስከፍላሉ፤የማስታወቂያው ዘርፍ  ከወዲሁ በህግ እና ሥርዓት ካልተመራ  ፍትሀዊ የንግድ ውድድርን ይጎዳል ህብረተሰቡንም ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች ይዳርጋል ብለዋል፡፡

ስለሆነም ህብረተሰሰቡ ለተለያዩ ችግሮች ከመዳረጉ በፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመቀነስ ቅንጅታዊ አሰራር ያስፈልጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፤በአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቂያ  እና ተያያዥ ጉዳዮች  ዙሪያ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጩ ማስታወቂያዎችን በህግ እና ሥርዓት መምራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብሩክ ታየ በበኩላቸው ካሁን በፊት በነበረን ግንኙነት ከተቋሙ ጋር በትብብር መስራታችን በዘርፉ የሚከሰቱ ችግሮችን መቀነስ መቻሉን ገልፀው ይህን የቆየ ግንኙነታችንን በሰነድ የተደገፈ ማድረጋችን ደግሞ ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር ወደፊት ከዚህ የተሻለ ስራ እንድንሰራ ያግዛል ብለዋል፡፡

በስምምነቱ ወቀት ሁለቱ ተቋማት ለማስታወቂያ እና ለመገናኛ ብዙኃን  ባለሙያዎች በማስታወቂያ ዘርፍ  የግንዛቤ ማስጨበጫ  ስራ እና ሌሎች ተየያዥ ጉዳዮች ዙሪያ  በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡