የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን ለሚዘግቡ ጋዜጠኞች የመግቢያ ባጅ እየሰጠ ይገኛል

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን ለሚዘግቡ ጋዜጠኞች የመግቢያ ባጅ እየሰጠ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን  ከኢፌዲሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር 37ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ  እና 44ኛውን የስራ አስፈፃሚዎች ስብሰባን ለመዘገብ ለሚመጡ  የውጭ  እና የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች  የመግቢያ  ባጅ (press pass) በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ባለሥልጣኑ የመግቢያ ባጅ ከመስጠት  በተጨማሪ ለሚዲያ አካላት የተለያዩ ምቹ ሁኔታዎችን  በመፍጠር ላይ ሲሆን፤ በተለይም   ከውጭ ለሚመጡ ጋዜጠኞች  ይዘዋቸው ለሚመጡ የዘገባ መሳሪያዎች ከቀረፅ ነፃ እንዲያስገቡ እና  የቪዛ አገልግሎት እንዲያገኙ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከጉምሩክ፣ ከአፍሪካ ህብረት ጋር እና ከሌሎች ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር እየሰራ ይገኛል፡፡

 እስካሁን ባለው ሂደት በጉባዔው ላይ ተገኝተው የሚዲያ ሽፋን ለመስጠት  ከ1 ሺህ በላይ የሀገር ዉስጥ እና የዉጭ ጋዜጠኞች ስብሰባውን ለመዘገብ ያመለከቱ ሲሆን ባለሥልጣኑ ሁሉም ጋዜጠኞች የመግቢያ ባጁን እንዲያገኙ የ24 ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

በቀጣይም  ጉባዔው እስከሚጠናቀቅ ድረስ በቦሌ ኤርፓርትና በአፍሪካ ህብረት በሚገኙ ጊዜያዊ ቢሮዎቹ እንዲሁም  በባለሥልጣኑ ዋና መስሪያ ቤት ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።