ባለሥልጣኑ ለበይነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ባለሥልጣኑ ለበይነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን  በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ  መከላከያ መንገዶች ዙሪያ ለበይነመረብ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች  እና  አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የባለሥልጣኑ /ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ  በባለሥልጣኑ ተመዝግበው በስራ ላይ የሚገኙ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከልና መቆጣጠር ላይ እንዲሁም እርስ በእርስ ቁጥጥርን በማጠናከር ረገድ ግንዛቢያቸውን እንዲያዳብሩ ለማስቻል መድረኩ እንደተዘጋጀ ተናግረዋል፡፡ አቶ ግዛው አክለውም  ባለሥልጣኑ ከበይነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን ማህበር ጋር  ወደፊት የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል ዘርፈ ብዙ  ስራዎችን ይሰራል ብለዋል፡፡

ስልጠናው የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ምንነት፣ የማህበራዊ ሚዲያ ባህሪያት፣ እውነትን ማጣራት (fact-check) እና የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን በመከላከል ረገድ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ሚና  እንዲሁም የእርስበርስ ቁጥጥር ሂደት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን በመከላከል ረገድ ከባለሥልጣኑ  እና ከሌሎች አካላት ጋር በመተባበር በትጋት እንደሚሰሩ ገልፀው  የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን ማህበሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

በሀገራችን በአሁኑ ሰዓት  በባለሥልጣኑ ተመዝግበው   ፈቃድ የወሰዱ 63 የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን ይገኛሉ።