የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች ዙሪያ  ስልጠና ሰጠ፡፡

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች ዙሪያ  ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች ዙሪያ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ  ስልጠና ፈላጊዎች የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱ አሊ ስልጠናውን በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት ባለሥልጣኑ በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የዜጎችን ተሳትፎ እና የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት /Media literacy/ የሚያሳድጉ ዘዴዎችን ቀይሶ እየሰራ ይገኛል። ከነዚህ ዘዴዎች አንዱ  የፊት ለፊት ስልጠና ነዉ ብለዋል።

በዚህ የዲጅታል ዘመን መረጃ በሁሉም አቅጣጫ ይፈሳል ሆኖም ሁሉም መረጃ ጠቃሚ እና ትክክለኛ አይደለም፤ ትክክለኛዉን ከሐሰተኛዉ ለመለየት የሀቅ ማጣራት / fact cheking/ ክህሎት  አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ሥልጠና ተዘጋጅቷል ያሉት አቶ አብዱ ይህን ስልጠና ስታጠናቅቁ ክህሎታችሁን ከማሳደግ ባለፈ ባለሥልጣኑ ለሚያከናዉናቸዉ ስራዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አጋዥ  እንደምትሆኑ እናምናለን ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል።

ሰልጣኖች በበኩላቸው ስልጠናው በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች ዙሪያ ክህሎታቸውን በማሳደግ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የሚለቀቁ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃዎችን በቀላሉ እንድንለይ ያግዘናል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨትና ከማጋራት ተቆጥበን የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ሂደት የበኩላችንን አስተዋፅኦ እንድንወጣ የሚያስችል ግንዛቤ ፈጥሮልናል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዜጎች ራሳቸዉን፣ ቤተሰባቸዉን ብሎም ሀገራቸዉን ከሐሰተኛ መረጃ እንዲከላከሉ  ለማስቻል የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ባለሥልጣኑ  ዜጎች  የሚያጋጥማቸዉን የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃዎች፣ በመገናኛ ብዙኃን ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት እና የሙያ ስነ ምግባር ጉድለት የሚጠቁሙበት 9192 ነፃ የስልክ መስመር ዘርግቶ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል።