የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የማስተባበር ስራ ላከናወኑ ባለሙያዎች የምስጋና መርሃ ግብር አካሄደ፡፡

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የማስተባበር ስራ ላከናወኑ ባለሙያዎች የምስጋና መርሃ ግብር አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር 37ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛውን የአስፈፃሚዎች ም/ቤት ስብሰባ ለመዘገብ የመጡ ጋዜጠኞችን ላስተባበሩ ለተቋሙ ባለሙያዎች የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በትብብር መስራት የተቋሙን ተልዕኮ እውን ከማድረግ አንፃር  የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰው ባለሙያዎቹ በአፍሪካ ህብረት ጉባዔ ያሳዩት የስራ ተነሳሽነት እና ትብብር ውጤታማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

በጋራ እና በትብብር መስራት የተቋሙን ተልዕኮ ከማሳካት ባሻገር ሀገርን መገንባት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በቀጣይም በዚህ ስራ ላይ የታየውን የትብብር መንፈስ በተሻለ ተሞክሮ በመቀመር  አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል፡፡

በመርሃ ግበሩ ባለሥልጠኑ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን መዘገብ ለመጡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ባደረገው ተሳትፎ ዙሪያ ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በሪፖርቱ ላይም  ጉባዔውን ሽፋን ለመስጠት ለተመዘገቡ 1052 የሚዲያ አካላትና ጋዜጠኞች  ሙሉ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከውጭ ለገቡ ለ386 ጋዜጠኞች የቪዛ አገልግሎት እንዲሁም በኢምባሲ በኩል ለመጡ ለ93 ጋዜጠኞች የሙያ መሳሪያቸውን ከቀረፅ ነፃ ይዘው እንዲገቡ መደረጉ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መገናኛ ብዙኃን እና ጋዜጠኞች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል በቦሌ ኤርፖርት፣ በአፍሪካ ህበረት እንዲሁም በዋናዉ ቢሮ የ24 ሰዓት አገልግሎት በመስጠት የ37ኛዉ  የአፍሪካ ህበረት ጉባዔ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ መደረጉ ተገልፆል፡፡

በመጨረሻም የ37ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላስተባበሩ እና የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ ላበረከቱ የተቋሙ ባለሙያዎች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል፡፡