Asset Publisher

ዜናዎች

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ኦን ፕሮሞሽን ኃ/የተ/የግ/ማ (On promotion PLC) በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካሄደው አለም አቀፉ የሚዲያ ኤክስፖ በጋራ ለማዘጋጀት በዛሬው እለት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ በስምምነቱ ወቅት እንደተናገሩት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚዲያውን ዘርፍ የሚያሳድጉ ኤክስፖዎች በተለያዩ ሀገራት ይካሄዳሉ፤ በሀገራችን ደረጃም አሁን መጀመሩ ለሚዲያው እድገት ትልቅ እምርታ ነው። ስለሆነም ቀጣይነት ባለው መልኩ በትብብር እንሰራለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በተቋሙ የ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ።

በውይይቱ የሩብ ዓመቱ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በእቅድ የተያዙ ስራዎች አፈጻጸማቸው ምን እንደሚመስል እንዲሁም የተገኙ ጠንካራ ጎኖች እና የተስተዋሉ ክፍተቶች በሪፖርቱ ተነስተዋል። ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ እንዲጠናከሩ እና የታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ደግሞ የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች የተለያዩ አስተያየቶችን በማንሳት እንዴት ማሻሻል እንደሚገባ እና ወደፊት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከUN WOMEN ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሥርዓተ ጾታ ምላሽ ሰጭ መመሪያ ዙሪያ እና የሴቶችን የውሳኔ ሰጪነት ሚናን ለማጎልበት የሶስት ቀን ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

የስልጠናው ዋና አላማ ሥርዓተ-ጾታን ያገናዘበ ምላሽ ሰጭ መመሪያ አተገባበር፤ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ሴት እና ወንድ ባለሙያዎች ስለሚያገኟቸው እና ስለሚያሰጧቸው ዕድሎች፤ መገናኛ ብዙኃን በይዘታቸው ወንዶች እና ሴቶችን የሚዘግቡበትና የሚቀርጹበት ዕይታ፤ የጋዜጠኞች ዘገባዎች የሁለቱም ጾታዎች ድምጽ እና ሃሳብ በእኩል መጠን ማስተናገድ ዙሪያ ላይ አቅም መገንባት ያተኮረ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የኤፍ.ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ ፕሮግራሞችን በቀጥታ ተቀብለው ማስተላለፍ ወይም ሊንክ ማድረግ ከዛሬ ጀምሮ የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የሬዲዮ ሞገድ በሀገራችን በጣም ውስን መሆኑ ይታወቃል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሬድዮ ባለፈቃዶች በማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እንዲሁም የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ይዘቶችን በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ መረጃ ተደራሽ ማድረግ አለባቸው። 

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ፍትህ ለሁሉም ኢትዮጵያ (Justice for All - P.F.E) በመገናኛ ብዙኃን እድገት ዙሪያ በጋራ ለመስራት በዛሬው ዕለት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

ተቋማቱ ከዚህ በፊት የሚዲያ ኢንዱስትሪውን እድገት አስመልክቶ የጋራ ጥናት አካሂደዋል፡፡ በመሆኑም በጥናቱ በተለዩ ጉዳዮች፣ በሚዲያ ሕጎችና አሰራሮች እንዲሁም በሚዲያ አቅም ግንባታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢንተርናሽናል ሚዲያ ሰፖርት (IMS) አለም አቀፍ ድርጅት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

አይ. ኤም. ኤስ. (IMS) ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጋር የተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ በትብብር የሚሰራ አለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን ተቋሙ ከባለሥልጣኑ ስር ከሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ክትትል(የሞኒተሪንግ) ክፍሎች ጋር በመሆን የክትትል ስራን ለማሳደግ፣ ለማዘመን እና የመገናኛ ብዙኃን ኢንዱስትሪውን ለማብቃት ከባለሥልጣኑ ጋር እየሰሩ እንደሆነ በውይይቱ ተገልጿል፡፡

 

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም(UNDP) ኃላፊዎች የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን ጎበኙ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የእርስበርስ ግንኙነትና ትብብር እንዲጠናከርና የመገናኛ ብዙኃን ኢንዱስትሪን ለማጎልበት እንዲሁም ከዚህ በፊት ላበረከቷቸው አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ባለሥልጣኑን ጎብኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከግል መገናኛ ብዙኃን ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዉና ነበራዊ ሁኔታ ላይ ምክክር አደረገ

“ሃገርን ለማዳን ተልዕኮ ወስዶ መስራት ለህዝብ ያለን ወገንተኝነት ማሳየት ነው፡፡ይህ ግዜ ወገንተኝነታችንን የምናሳይበት ሰዓት ነው፡፡ ስሙ የግል ይሁን እንጂ ሚዲያ የህዝብ ሃብት መሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው” አቶ መሃመድ ኢድሪስ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር

አንጋፋ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን እድገት ፍኖተ-ካርታ ላይ ምክክር አደረጉ

ለረጅም ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ የቆዩ አስር አንጋፋ ባለሙያዎች እና ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የእድገት የሃሳብ ፎኖተ-ካርታ ላይ ምክክር እደርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሰራተኞች የችግኝ ተከላ አካሄዱ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣የኢፌድሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የፌደራል ዋና ኦዲተር መ|ቤት በጋራ በመሆን በሆለታ ከተማ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራቶኞች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለገሱ፡፡

ለሃገር አንድነትና ሉዓላዊነት በዱር በገደሉ ደሙን እያፈሰሰና አጥንቱን እየከሰከሰ ኢትዮጵያና ልጆቿን እየጠበቀ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከሙያዊ ድጋፋቸው በተጨማሪ የአንድ ወር ደሞዛቸውን በመለገስ ከጎኑ መሆናችውን አሳይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራቶኞች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ አደረጉ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለሃገር አንድነትና ሉዓላዊነት የሚከፍለው ዋጋ ታሳቢ አድረገው በማንኛውም ግዜና ሁኔታ ከጎኑ መሆናቸውን ለመግለፅ ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን 2013 ዓ.ም የደም ልገሳ አካጊሂደዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር አና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን የሚከታተልበትን የጥሪ ማዕከል ገንብቶ ስራ ላይ አዋለ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከታተል የሚያስችለውን የቅሬታና እና ጥቆማ መቀበያ የጥሪ ማዕከል ገንብቶ ስራ ጀምሯል

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በ2013 እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በ2014 ዓ.ም የእቅድ አቅጣጫ ዙሪያ ሰረተኞቹን እያወያየ ይገናኛል

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በ2013 እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በ2014 ዓ.ም የእቅድ አቅጣጫ ዙሪያ ሰረተኞቹን እያወያየ ይገናኛል

አንጋፋ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን እድገት ፍኖተ ካርታ ላይ ምክክር አደረጉ

አንጋፋ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን እድገት ፍኖተ ካርታ ላይ ምክክር አደረጉ

መገናኛ ብዙሃን ሙያዊ ስነ-ምግባርን ባከበረና ከፍ ባለ አገራዊ ስሜት ለሰሩት ዘገባ ምስጋና ይገባቸዋል

መገናኛ ብዙሃን የምርጫውን ሂደት ሙያዊ ስነ-ምግባርን ባከበረና ከፍ ባለ አገራዊ ስሜት መዘገባቸው የሚያስመሰግን ተግባር መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለመገናኛ ብዙኃን የሰጡት ቃለ-መጠይቅ ከምርጫው በፊት እንዳይተላለፍ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አሳሰበ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን የሰጡት ቃለ መጠይቅ በዚህ የጥሞና ወቅት በመገናኛ ብዙኃን እንዳይተላለፍ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ማሳሰቡን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስታዉቋል።

ዓለም ፐሬስ ነፃነት ቀን ለ30ኛ ግዜ "መረጃ ለህዝብ ጥቅም" በሊል ርዕስ ሲከበር ይውላል፡፡

ዓለም ፐሬስ ነፃነት ቀን ለ30ኛ ግዜ "መረጃ ለህዝብ ጥቅም" በሊል ርዕስ ሲከበር ይውላል፡፡ ባለድርሻ አካላት ላይት ሆቴል በተዘጋጀው ኮንፍረንስ ተሰባስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ገለልተኛ የህግ አርቃቂ ቡድን ያዘጋጃውን የመገናኛ ብዙኃን መመሪያዎች ለውይይት አቀረበ፡፡

ለውይይት የቀረቡት አራቱ መመሪያዎች የንግድ፣ የህዝብ፣የበይነ-መረብ የማህበረሰብ እና ልዩ የህዝብ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት መመሪያዎች ናቸው፡፡

የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን ለ30ኛ ግዜ "መረጃ ለህዝብ ጥቅም" በሊል ርዕስ እየተከበረ ይገኛል፡፡

የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን ለ30ኛ ግዜ "መረጃ ለህዝብ ጥቅም" በሊል ርዕስ እየተከበረ ይገኛል፡፡ 

— 30 Items per Page
Showing 31 - 50 of 50 results.