ባለሥልጣኑ ለሰራተኞቹ ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ባለሥልጣኑ ለሰራተኞቹ ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ለሰራተኞቹ  ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናውን የከፈቱት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ እንዳሉት የሥልጠናው ዓላማ ሁሉም የባለሥልጣኑ ሰራተኞች ጥሩ የስራ ባህልን እንዲገነቡ ለማስቻል እና ለስራ እንዲነሳሱ እንዲሁም ብቁ ሰራተኞች ሆነው ሀገርን እንዲያገለግሉ ለማስቻል ያለመ ነው ብለዋል።

 

አቶ መሐመድ አክለውም የምትወስዱት ስልጠና አስተማሪና ተነሳሽነትን የሚፈጥር በመሆኑ በተግባር በመቀየር ልትጠቀሙበት ይገባል ሲሉ ለሰራተኞቹ አሳስበዋል፡፡