የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአረብኛ ቋንቋ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ስልጠና ሰጠ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአረብኛ ቋንቋ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ስልጠና ሰጠ፡፡


የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከአልጀዚራ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ውስጥ በአረብኛ ቋንቋ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል፡፡


የስልጠናው ዋና ዓላማ በአረብኛ ቋንቋ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ዜናዎችን እንዴት መስራት እንዳለባቸው፣ የዜና ምንጫቸውን በሚገባ እንዲያውቁና የጋዜጠኝነት የስነ-ምግባር መርህን ተከትለው እንዲሰሩ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡


የኢ.መ.ብ.ባ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ ሰልጣኞቹ የተለያዩ ዘገባዎችን በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በተገቢው ሁኔታ በመዘገብ ለቋንቋው ተናጋሪዎች ተደራሽ ለማድረግና ለማስገንዘብ ስልጠናው እንደሚያግዛቸው ገልፀው ወደፊትም የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር በተከታታይ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎቸን በመስጠት የማገዝ ስራዎችን እንሰራለን ብለዋል፡፡ 


ሰልጣኞቹም የሙያ ስነ-ምግባሩን በመከተል የሙያ ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አቶ ዮናታን  ጨምረው አሳስበዋል፡፡

https://twitter.com/YonatanTR