ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለመገናኛ ብዙኃን የሰጡት ቃለ-መጠይቅ ከምርጫው በፊት እንዳይተላለፍ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አሳሰበ!

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን የሰጡት ቃለ መጠይቅ በዚህ የጥሞና ወቅት በመገናኛ ብዙኃን እንዳይተላለፍ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ማሳሰቡን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስታዉቋል። ባለሥልጣኑ አክሎም በማሕበራዊ ሚዲያዎችም እየተላለፉ ያሉ የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስሉ መልዕክቶችም በአስቸኳይ ሊቆሙ እንደሚገባ አስሳስቧል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ምንም እንኳን ቃለ መጠይቁ የመንግስት የስራ ክንውኖች ላይ ያተኮረና የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልሆነ ቢታወቅም በዚህ የጥሞና ወቅት ሊተላለፍ አይገባም ብለዋል። የቃለ-መጠይቁ መተላለፍ ብዥታ እንዳይፈጥር ሲባል ከምርጫው በፊት መተላለፍ እንደሌለበትም አቶ መሀመድ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ቃለ-መጠይቁ እንዳይተላለፍ የተፈለገው መንግስት በዚህ ዓመት የሚካሄደው ምርጫ ፍትሀዊ እንዲሆን ፍላጎት ስላለው መሆኑን አስረድተዋል። ስለዚህ ቃለ-መጠይቁን ለማስተላለፍ ማስታወቂያ እየሰሩ ያሉ መገናኛ ብዙኃንም ሆኑ ለማስተላለፍ የተዘጋጁ ከወዲሁ እንዲያቆሙ አሳስበዋል።

መገናኛ ብዙኃንም ቢሆኑ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በመጠናቀቁ ቅስቀሳ መሰል ዘገባዎችን ከማስተላለፍ ሊጠነቀቁ ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባወጣው የሰዓት ድልድል መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች መገናኛ ብዙኃንን ተጠቅመው የተሳካ ቅስቀሳ ሲያደርጉ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል።