ራዕይ

ራዕይ

  • 2022 የሕግ የበላይነትን እና የሙያ ስነ-ምግባርን ያከበረ የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ዘርፍ እውን ሆኖ ማየት፤

ተልዕኮ

  • በአስቻይ ቁጥጥር፣ አቅም ግንባታ እና አጋርነት ብዝኃነቱ የተረጋገጠ እና በኃላፊነት የሚሰራ የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ዘርፍ ማጎልበት፤

እሴት

  • ገለልተኝነት
  • ተጠያቂነት
  • ትብብር
  • የሙያ ልህቀት

Asset Publisher

null ባለሥልጣኑ ለሰራተኞቹ ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

ባለሥልጣኑ ለሰራተኞቹ ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ለሰራተኞቹ  ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናውን የከፈቱት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ እንዳሉት የሥልጠናው ዓላማ ሁሉም የባለሥልጣኑ ሰራተኞች ጥሩ የስራ ባህልን እንዲገነቡ ለማስቻል እና ለስራ እንዲነሳሱ እንዲሁም ብቁ ሰራተኞች ሆነው ሀገርን እንዲያገለግሉ ለማስቻል ያለመ ነው ብለዋል።

 

አቶ መሐመድ አክለውም የምትወስዱት ስልጠና አስተማሪና ተነሳሽነትን የሚፈጥር በመሆኑ በተግባር በመቀየር ልትጠቀሙበት ይገባል ሲሉ ለሰራተኞቹ አሳስበዋል፡፡