የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ጋር ውይይት አካሄደ ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ጋር ውይይት አካሄደ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25 2014 (...)

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ  የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር "የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለአብሮነት እሴቶች መጠናከር" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

የውይይት መድረኩ ዓላማ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የሚያሰራጯቸው ይዘቶች በሀገራችን ተከብሮ የቆየውን የሃይማኖት መቻቻልና አብሮነት ለማጠናከር እንዲሁም በሰላም እሴቶች ግንባታ ላይ ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን  ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ  እንዳሉት የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ግብረ ገብነትን በማስተማር ትውልድን ከማነፅ በተጨማሪ የጋራ እሴቶች እንዲጠናከሩ፣ አብሮነት እና ወንድማማችነት እንዲጎለብት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

ስለሆነም የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን በአስተምሮታቸው አሁን ላለንበት ችግር መፍትሄ በሚያመጣ ሀገር በሚገነባና መልካም ዜጋን በሚያንፅ  ጉዳይ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የአብሮነት አሴቶችን በማጠናከር እና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ሊጫወቱት ስለሚገባው ሚና እንዲሁም የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የህግ ማዕቀፎች የሚሉ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመጨረሻም ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለምዝገባ የሚየስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን   አሟልተው ምዝገባ ላከናወኑ 23 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የምዝገባ ሰርተፊኬት የመስጠት ስነ-ስርዓት ተከናውኖ ውይይቱ ተጠናቋል።