ራዕይ
ራዕይ
- በ2022 የሕግ የበላይነትን እና የሙያ ስነ-ምግባርን ያከበረ የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ዘርፍ እውን ሆኖ ማየት፤
ተልዕኮ
- በአስቻይ ቁጥጥር፣ አቅም ግንባታ እና አጋርነት ብዝኃነቱ የተረጋገጠ እና በኃላፊነት የሚሰራ የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ዘርፍ ማጎልበት፤
እሴት
- ገለልተኝነት
- ተጠያቂነት
- ትብብር
- የሙያ ልህቀት
Publicador de contenidos
ባለሥልጣኑ በቴከኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓትን ከመዘርጋት እና ከሰው ሃብት ስምሪት አንፃር የሰራቸው ስራዎች ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቆመ፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው ምልከታ ባለሥልጣኑ በቴከኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓትን ከመዘርጋት እንዲሁም ከሰው ሃብት ስምሪት አንፃር የሰራቸው ስራዎች ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተመላክቷል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው በባለሥልጣኑ በመገኘት የተለያዩ የስራ ክፍሎችን የጎበኘ ሲሆን በምልከታው ባለሥልጣኑ ከአሰራር ስርዓት ዝርጋታ፣በቴክኖሎጅ በመታገዘ ስራን ከማቀላጠፍ አንፃር እንዲሁም ከሰው ሃይል ስምሪት አንፃር ያመጣው ለውጥ አበረታች እና ተሞክሮ ሊሆን የሚችል በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ እውነቱ አለነ ባለሥልጣኑ የሚያከናውናቸው የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች፣ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ሂደት እንዲሁም የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት በቴከኖሎጂ የታገዘ እና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እየተከናወነ ያለ መሆኑ ሊበረታታና ሊቀጥል የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡
ባለሥልጣኑ በጥራትና በቴክኒሎጂ በታገዘ መልኩ በመስራት የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫ ለማሳካት የጀመራቸው ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉና ለሌሎች ተቋማትም ተሞክሮ ሊሆኑ የሚገባቸው መሆናቸውንም ሰብሳቢው ጨምረው ተናግረዋል፡፡
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው ቋሚ ኮሚቴው የባለሥልጣኑን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘቱ አመስግነው የአቅም ግምባታ ስራን እንዲሁም ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አሰራርን በማዘመን ረገድ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃርም ከግንዛቤ ፈጠራ ስራ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡