Publicador de contenidos

service

 

አገልግሎት

ema
ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት

ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት

ema
ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ

የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ይዘት ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ

ema
የአቅም ግንባታ መስጠት

ለመገናኛ ብዙኃን እና ለማስታወቂያ ዘርፍ የአቅም ግንባታ መስጠት

ema
ጥናቶችን መሰራት

የዘርፉን እድገት እና ለውጥ ለማጠናከር የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን መሰራት

Publicador de contenidos

null ባለሥልጣኑ በቴከኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓትን ከመዘርጋት እና ከሰው ሃብት ስምሪት አንፃር የሰራቸው ስራዎች ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቆመ

ባለሥልጣኑ በቴከኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓትን ከመዘርጋት እና ከሰው ሃብት ስምሪት አንፃር የሰራቸው ስራዎች ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቆመ፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው ምልከታ ባለሥልጣኑ በቴከኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓትን ከመዘርጋት እንዲሁም ከሰው ሃብት ስምሪት አንፃር የሰራቸው ስራዎች ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተመላክቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በባለሥልጣኑ በመገኘት የተለያዩ የስራ ክፍሎችን የጎበኘ ሲሆን በምልከታው ባለሥልጣኑ ከአሰራር ስርዓት ዝርጋታ፣በቴክኖሎጅ በመታገዘ ስራን ከማቀላጠፍ አንፃር እንዲሁም ከሰው ሃይል ስምሪት አንፃር ያመጣው ለውጥ አበረታች እና ተሞክሮ ሊሆን የሚችል በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ እውነቱ አለነ ባለሥልጣኑ የሚያከናውናቸው የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች፣ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ሂደት እንዲሁም የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት በቴከኖሎጂ የታገዘ እና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እየተከናወነ ያለ መሆኑ ሊበረታታና ሊቀጥል የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ባለሥልጣኑ በጥራትና በቴክኒሎጂ በታገዘ መልኩ በመስራት የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫ ለማሳካት የጀመራቸው ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉና ለሌሎች ተቋማትም ተሞክሮ ሊሆኑ የሚገባቸው መሆናቸውንም ሰብሳቢው ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው ቋሚ ኮሚቴው የባለሥልጣኑን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘቱ አመስግነው የአቅም ግምባታ ስራን እንዲሁም ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አሰራርን በማዘመን ረገድ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃርም ከግንዛቤ ፈጠራ ስራ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

pricestyle

getintouch

ማንኛውንም ቅሬታ ወይም አቤቱታ ለማቅረብ

broadcaster

 

በባለሥልጣኑ የተመዘገቡ ብሮድካስተሮች በቁጥር

20
የህዝብ መገናኛ ብዙኃን
38
የንግድ ብሮድካስተር
56
የማህበረሰብ ብሮድካስተር
3
ሰብስክሪብሽን